1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዉሳኔ

ረቡዕ፣ መጋቢት 11 2016

እስራኤል በጋዛ እየወሰደችው ካለው እርምጃ አንጻር የህብረቱና የእስራኤል የጋራ ትብብር ውል እንዲከለስ ቀደም ሲል በአየርላንድና ስፔን ተጠይቆ፤ ብዙም ተቀባይነት ያልነበረው ሀሳብ፤ ባሁኑ ወቅት የብዙዎቹን ድጋፍ እግንቶ ክርክር እየተደረገበት እንደሆነም ሚስተር ቦርየል አስታውሰዋል ።

https://p.dw.com/p/4dw5I
ቦሬል የመሩት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ለዩክሬን ተጠማሪ 5 ቢሊዮን ዶላር እንዲሰጥ ወስኗል።
የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ ዮሴፍ ቦሬል ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡምስል Alexandros Michailidis/European Union

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዉሳኔ

 

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ሰኞ ብራስልስ-ቤልጂግ ዉስጥ ባደረጉት ስብባ ስብሰባ፤ በዩክሬንና በጋዛ ጦርነቶች ላይ ትኩረት ሰጥተዉ ተወያይተዋል።ሚኒስትሮቹ ከሁለቱ አካባቢዎች በተጨማሪ በቀዉስና ሥርዓተ አልበኝነት ሥለምትናጠዉ ሐይቲ አስተዉ ተነጋግረዋል።የካረቢኳ ሐገር ሐይቶ ለዘመኑ የአገር መፍረስና የመንግስት አልባነት ምንነትንና መዘዙን ለማሳየት እንደ አብነት እየተጠቀሰች ነዉ።

በዩክሬን ላይ የተላለፉ ውሳኔዎች

በዩክሬን ጉዳይበተካሄደው ውይይት ሚኒስትሮቹ ሁለት ውሳኔዎችን ማሳላፋቸውን የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊና የስብሰባው መሪ ሚስተር ጆሴፕ ቦርየል በጋዜጣዊ መገለጫቸው ይፋ አድርገዋል። “ አንደኛ ለዩኪሬን መርጃ የቀረበውን አምስት ቢሊዮን ኢሮ አጽድቀናል። ሁለተኛ በአሌክሲ ናቫንሊ ግድያ ተጠያቂ በሆኑ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ተስምምተናል” በማለት  ለዩክሬን የሚስጠው እርዳታ መጽደቁ  ህብረቱ ለዚች አገር የሚስጠውን እርዳታ ተገማችና አስተማማኝ የሚያደርገው መሆኑን ገልጸዋል። ብስብሰባው  ፕሬዝዳንት ፑቲን ለአምስተኛ ግዜ አሸናፊ የሆኑበት የሩሲያ ምርጫ  ምንም አይነት የዴሞክራሲያዊ ምርጫ መስፈርትን የማያሟላ ነውም ተብሏል። በህይል በተያዙ የዩክሬን ግዛቶች ምርጫ መደረጉ ደግሞ ሁለተኛ ወንጀል ነው ብለዋልም ሚስተር ቦርየል በጋዜጣዊ መግለጫቸው። በተጨማሪም በእስር ላይ እንዳለ ህይወቱ ያለፈውና የሩሲያ ተቃዋሚ  የነበረው ሚስተር አሌክሲ ናቫንሊ ግድያ ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ በተባሉ 30 ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ከስምምነት የተደረሰ መሆኑም ተገልጿል።

የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮቹ ባሁኑ ስብሰባቸዉ የዩክሬን፣ የጋዛና የሐይቲን ወቅታዊ ጉዳይ አንስተዉ ተነጋግረዋል።
የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ሲደረግ ብራስልስ-ቤልጂግምስል Alexandros Michailidis/European Union

የሚኒስትሮቹ ስብሰባ አሳሳቢ በሆነው የጋዛ ርሀብ ላይ   

የመካከለኛው ምስራቅን በሚመለክት፤ሚኒስትሮቹ በተለይ 2.2 ሚሊየን በሚሆነው የጋዛ ህዝብ ላይ ያንዣበበበውን የረሀብ አደጋና እልቂት የመንግስታቱ ድርጅት ተወካይ ባአስረጅነት በተገኙበት ተወያይተዋል። ሚስተር ቦርየል በስብሰባው እለት የአለም የምግብ ድርጅት በፍልስጤም ስላለው ሁኔታ ያወጣውን ርፖርት በመጥቀስም፤ ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ወይም መቶ ፐርሰንት በችግር ላይ መሆኑንና 70 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ በረሀብ አደጋ ላይ መሆናቸውን አውስተዋል። ቀደም ሲል ወደ ስብሰባው ሲገቡም የጋዛን ሁታ እንዲህ በማለት ነበር ለመገናኛ ብዙሀን  የገለጹት፤ “ ጋዛ ከጦርነቱ በፊት ግልጽ እስርቤት ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ግልጽ የጅምላ መቃብር ሁኗል;። የጅምላ መቃብር ለሰውም ለአለማቀፍ ህግና ሰባዊነትም”። ሚኒስትሮቹ የርሀቡን አድጋ ለመቀልበስ እርዳታ ባስቸኳይ ለተረጂዎች መድረስ እንዳለበትና ለዚህም እስራኤል ሁኒታዎችን ማመቻቸትና መፍቀድ የሚገባት መሆኑን አሳስበዋል።
የህብረቱና የእስራኤል የትብብር ስምምነት እንዲከለስ መጠየቁ
በህማስ ላይ ሊጣል ስለሚገባው ማዕቀብ የተወያዩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ በአክራሪ እስራኤላውያን ሰፋሪዎች ላይም ማዕቀብ ለመጣል የፖለቲካ ስምምነት መኖሩን ሚስተር ቦርየል አስታውቀዋል። እስራኤል በጋዛ እየወሰደችው ካለው እርምጃ አንጻር የህብረቱና የእስራኤል የጋራ ትብብር ውል እንዲከለስ ቀደም ሲል በአየርላንድና ስፔን ተጠይቆ፤ ብዙም ተቀባይነት ያልነበረው ሀሳብ፤ ባሁኑ ወቅት የብዙዎቹን ድጋፍ እግንቶ ክርክር እየተደረገበት እንደሆነም ሚስተር ቦርየል አስታውሰዋል ።

የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፅሕፈት ቤት የአባል ሐገራቱ አንድነት ምሳሌም ተደርጎ ይታያል
የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ዋና መቀመጫና የሕብረቱ አርማ-ብራስልስ-ቤልጂግምስል James Arthur Gekiere/dpa/Belga/picture alliance

ሀይቲ የፈረሰ ሀገር ተምሳሌት
 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በዚህ ስብሰባቸው መንግስቷ ፈርሶ ስራተአልበኝነት ነግሶ በወረበሎች እጅ የወደቀችውንየሀይቲንሁኔታም ትኩረት ስቶ ተወይይቱል። ወደ አካባቢው የፖሊስ ሀይል በመላክ ህግና ስራት በማስክበር መንግስታዊ ስራቱን ለማስመለስ በሚደረገው አለማቀፋዊ ጥረት ህብረቱ   የበኩሉን አስተውጾ ለማድረግ በሚችልባቸው ሁኒታዎች ላይም ምክክር መደረጉ ታውቋል። አገር ሲፈርስና መንግስት አልባ ሲሆን  ምን ሊመስልና ምን ሊፈጠር እንደሚችል ሀይቲ ጥሩ ማሳይ መሆኗን  የገለጹት ሚስተር ቦርየል፤ ስራት ሊያስጠብቅና ህግ ሊያስከብር የሚችል ሲጠፋ፤  አገር በወረበሎች እጅ ልትወድቅ፤ የርበርስ ጦርነት ሊከፈትና ስራተአልበኘነትም ሊነግስ  እንደሚችል አሁን ሀይቲ ያለችበት ሁኔታ የሚያረጋጥ ነው ብለዋል።  እንደዚህ አይነት ሁኒታ በሌሎች ቦታዎችም የታየበት ግዜ እንዳለና በጋዛም እንዳይከሰት የሚያሰጋ መሆኑንም አንስተዋል። “ ለከሸፈ መንግስትና ለወደቀ አገር ሀይቲ ጥሩ ምሳሌ ናት። እንደዚህ አይነት ሁኒታ በሶማሊያ ሞቃዲሾ ታይቷል።  በጋዛ ያለው ሁኒታ ወደዚያ የሚያመራ እንዳይሆንም ያሰጋል” በማለት የተፈጠረውን ቀውስ መጠቀም የሚፈልጉ ወረበሎችና  ወንጀለኞች እየታዩ በመሆኑ፤ አስፈላጊው ድጋፍ ካልተደረገና ህግና ስራት ካልተመለሰ ጋዛም የሜድትራኒያኗ ሀይቲ ልትሆን ትችላለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል። .

ገበያው ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ